top of page

መግቢያ
(Getting Started)
ይህንን ዌብሳይት ለመስራት ያነሳሳኝ ምክንያት የሜካፕ ስልጠና ሳልወስድ በፊት በጣም ሜካፕ ስጥቀም እቸገር ነበር። ዩቱብ ቻናሎች ላይ ብዙ ግዜዬን ኣጠፋ ነበር ከስንት እንዴ ነበር የሚሳካልኝ፤ ብዙውን ግዜ ለምን የኛ ኢትዮጵያውያን ኣልሰሩትም ብዬ እጠይቅ ነበር፤ ብዙ እህቶቼ እኔ እንደተቸገርኩ እንደምትቸገሩ እርግጠኛ ነኝ። ቆንጆዊት የሜካፕ ኣጠቃቀም ዌብሳይት ይህንን ችግር ለመቅረፍ በትንሹ ያግዛል ብዬ ተስፋ ኣደርጋለሁ።
ይህ ዌብሳይትን በመስራት ላይ እያለሁ የተለያዩ ዩቱዩብ ቻናሎች ላይ ኢትዮጵያዊ እህቶቼ በምስል የታገዘ ማብራሪያዎችን በማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት ሳላደንቅ ማለፍ አልፈልግም ምክንያቱም ሊበረታታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነውና። እኔ በጽሁፍ ደሞ የተለያዩ የውበት ምክሮችን በማከል አልፎ አልፎ አልፎ ደሞ በምስል የታገዘ ጽሁፌን አቀርባለሁ። በጽሁፍ ለማድረግ ያነሳሳኝ ጉዳይ የሃገራችን የኢንተርኔት አገልግሎት ብዙም አጥጋቢ ስላልሆና እህቶቼ ይሄ መንገድ ቀለል ይላል ብዬ ነው።
About: Inner_about
bottom of page
