top of page

ሜካፕ ለጥቁር ቆዳ ፊት እንዴት ነው የምንጠቀመው?

  • Jul 1, 2017
  • 2 min read

ሜካፕ እንዴት መጠቀም ማወቅ ይፈልጋሉ?

እያንዳንዱ የሜካፕ ጥበብ ስራ የሚጀምረው ከጥሩ ፋውንዴሽን (foundation) እና ፊትዎ ነው ምንም ከባድ ኣይደለም። ከቆዳዎ ቀለም ጋር የተመሳሰለ እና የተዋሃደ መሰረት ወይም ተፈጥሯዊ ውበትን ኣጉልቶ የሚያሳይ ነው።

ፋውንዴሽን (foundation) ሲመርጡ በችኮላ ሳይሆን በደንብ ጊዜ ወስደው መሆን ኣለብት የሚገዙበት ቦታ ናሙና የሚያስሞክሩ ቢሆን ይመረጣል ምክንያቱም በሚገዙ ጊዜ ናሙናውን በመንጋጋዎ መስመር ላይ ባለው ቆዳዎት ላይ ይሞክሩት፤ የሞከሩት ናሙና ከፊትዎ ላይ እየጠፋ ከሄድ ይሄ ለእርስዎ የቆዳ ቀለም የሚሆን ነው። ኣስታውሱ ዋናው ሊስተዋል የሚገባው ነገር እዚህ ላይ የተፈጥሯዊ ውበትን ኣጉልቶ ለማሳየት መሆን ኣለበት እንጂ በሜክአፕ መካከል ወፍራም ንብርብሮች ኋላ ሁሉንም ለመደበቅ እንዳልሆነ አስታውሱ።

ከዚህ በኋላ የምናየው እንዴት የማያስታውቅ አጨራረስ ለማግኘት በ ሜካፕ foundation, concealer እና powder ደረጃ ላይ ማስቀመጥ እንዴት ጠቃሚ ምክሮችን እስቲ እንመልከት.

እንዴት ሜካፕ ፋውንዴሽንን(foundation) ደረጃ በደረጃ ላይ ማስቀመጥ?

ማንኛውንም ፋውንዴሽን ሲጠቀሙ ወይም ተግባራዊ ሲያደርጉ በትክክለኛው መንገድ መደረግ ኣለበት። moisturizer ከተጠቀማችሁ በኋላ እነዚህን ቅድመ ተከተሎችን ያድርጉ፡ -

  1. በኣፍንጫዎ ላይ፣ በጉንጮችዎ ላይ፣ በኣገጭዎት እና ግምባርዎ ኣካባቢ ፋውንዴሽን (foundation)ነጥብ ነጥብ ያድርጉ ይህንን ለማድረግ ብሩሽ ወይም ስፖንጅ (sponge or brush)ይጠቀሙ፤ ብሩሽ ወይም ስፖንጅ (sponge or brush) ክሬም ወይም ፓውደር ለመጠቀም ይጠቅመናል።

  2. ንጹህ የእጆችዎን ጣቶች በመጠቀም በስፖንጅ ወይም በብሩሽ (sponge or brush)ወደ ላይ ወደ ታች እያደረጉ እያንዳንዱን የፊትዎን ግጽታ ይቀቡ ኣስታውሱ እያንዳንዱ የፊት ገጽታ ሽፋን መቀባቱን ያረጋግጡ።

  3. በደንብ ይቀላቅሉ ማለትም ከላይ 2ኛውን መንገድ በመጠቀም የፊትዎን ገጽታ ይለቅልቁት ይህንን ስል እንዳይጨማለቅቦት ተጠንቀቁ።

እዚህ ላይ አንድ ኣይነት ቀለም ወይም ከቆዳዎ ጋር መመሳሰሉን እያስተዋሉ ነው?

የተለያዩ ፋውንዴሽን(foundation)ለማንኛውም ወይም ለተለያዩ ቆዳ ቀለም ፍላጎት የሚያተኩሩ ኣሉ። ሜካፕ ለእርስዎ ቆዳ ቀለም በስተቀር ሌላ ምን ምን ነገር ሊያረግሎት ወይም ሊያገለግሎት እነደሚፈልጉ ያስቡ። ለምሳሌ:-

  • Hypoallergenic (ለስላሳ ቆዳ)

  • ሙሉ ሽፋን

  • ረጅም ቆይታ

  • ውሃ የማይሳልፍ

እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የተለያዩ ፋውንዴሽን(foundation) ስሪት ናቸው፡ -

  1. ፈሳሽ፡ - ከሶስቱ አይነቶች ደብዘዝ ካሉት ሽፋን ማግኛት ከፈለጉ በጣም ጥሩ ነው። ይህ በጣም በስፋት ቀን ላይ የሚጠቀሙበት ሜካፕ ነው። በእጅችዎ ጣት በሰፊው ፊትዎ ለማሰራጨት በጣም ቀላል ነው እና ይህም ከባድ አይደለም ሲጀመር ስህተቶችን ማድረግ አስቸጋሪ ነው::

  2. ከክሬም ወደ ፓውደር (Crème to Powder)፡ - ይሄኛው መካከለኛ ሽፋንን ያካትታል ምክንያቱም ይህ 'ሁሉም በአንድ' ነው የምርት አይነት ጉዞ ላይ ከሆኑ በጣም ጥሩ ምርት ነው። ይህ አይነቱ የሚያገለግለው ለቅባታማ የቆዳ አይነቶች ነው ይህም የሚርዳን ቆዳን ደረቅ አድርጎ ለብዙ ጊዜ እንዲቆይ ይረዳናል።

  3. ክሪም (Crème)፦ እነዚህ በዱላ እና በተደበላለቁ ቅርጾች የተሞሉና የተለመዱ ናቸው። ይህንን ሙሉ ፊት ሽፋን እንከን የሌለው ገጽታ ቢሰጥም በጥንቃቄ ካልተደረግ ሊበላሽቦት ይችላል።

ሜካፕ ሲጠቀሙ ዋናውና አንደኛ ሕግ የፋውንዴሽን ቀለም ለመሞከር ወይም ለመፈተን በተፈጥሮ ብርሃን መሆን አለበት። ምክንያቱም ትክክለኛውን የፊትዎን ቀለም ተዛማጅ ውጤት በቀላሉ ያገኛሉ።

ጠቃሚ ምክሮች ለእንከን አልባ ፋውንዴሽን (foundation) ትግበራ

  • ሜካፖን ፊትዎ ላይ ሲቀቡት ፊትዎና ሜካፖ መለየት እስኪያስቸግሮ ድርስ ያዋህዱት።

  • ወደ መንገጭላዎ እና የጸጉር መስመሮችዎ ላይ ልዩ ትኩረት ይስጡ

  • የአይን ሽፋኖችዎን በደንብ ያዋህዱት ይሄም የአይኖችዎን ሻዶው (shadow) በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲቆይና ቀለሞችን የበለጠ ግልጽ እና ያማሩ ይሆናሉ።

  • ሲጨርሱ ቲሹ ወረቀት ይያዙና በጥንቃቄ ቀስ እያሉ ማንኛውንም ትርፍ አስወግዱ።

 
 
 

Comments


Address

83 Lyndarum Dr
Epping, 3076
Australia

Contact

Follow

  • facebook

0488633789

©2017 BY KONJOWITE MAKEUP TUTORIAL. PROUDLY CREATED WITH WIX.COM

bottom of page