top of page

እንዴት ሜካፕ ኮንሲለር (Makeup Concealer) ደረጃ በደረጃ ላይ ማስቀመጥ

  • Jul 6, 2017
  • 2 min read

ሜካፕ ኮንሲለር (Makeup Concealer)

በጣም ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም እያንዳዳችን ከፊታችን ላይ ልንደብቀው የምንፈልገው ነገር ሊኖር ይችላል። ሊታይ የማንፈልገው ፊታችን ላይ ለምሳሌ ማዲያት፣ ሽታ፣ ጠባሳና የተለያዩ ሁኔታዎችን በደንብ ይሸፍንልናል። ይሄም ምርት ቁንጅናን አጉልቶ ይሰጠናል።

ደረጃ 1.ኮንሲለሩን (Concealer) የሚፈልጉበት የፊትዎ ሽፋን አካባቢ ላይ ነጥብ ነጥብ ያርጉ

ደረጃ 2. በእጆችዎ ጣት ወይም በስፖንጅ አሊያም በኮንሲለር (Concealer) ብሩሽ በቀስታ መታ ያድርጉት በሚፈልጉበት ቦታ ከዛም ወደ ላይ ወደ ታች ይቀቡት።

ደረጃ 3. በደንብ ይቀላቅሉት

የተለያዩ የኮንሲልር (Concealers) አይነቶች ምን ምን ናችው?

1. ክሬም ስቲክ (Cream Stick)፡ -ይህ በጣም ከባድና ቀለም ለመቀየር ምቹና ውበትን ያጎላል፤ ከቆዳዎ ጋር ለማዋሃድ በጣም አስቸጋሪ ነው ለዚህ ነው ይህ ምርት ውብ ቆዳ ላላቸው የማይሞከረው።

2. ፖት(Pot) : - ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል, ግን የተሻለ ውህድ እና የበለጠ እርጥበት ያለው ነው. ይሄ በዓይኖቹ ስር ለሆኑ አካባቢዎች ምርጥ ነው።

3. ቱዩብ(Tube)፡ -ክሬምና ከፊትዎ ጋር ለመዋሃድ በጣም ቀላል ነው፤ ይህ ምርት ቀለል ያለ ከፊትዎ ጋር ለማስለቀቅ ከፖት (Pot) ይልቅ ይሄኛው ይመረጣል።

4. ዋንድ(Wand)፡ -

ይህ በእጅ ለመያዝ ቀላልና ወደ ኪስ ቦርሳዎ ለመክተት መጠኑ አነስተኛ ነው።

5. እርሳስ(Pencil)፡ -ድንገት አንድ ቦታ ላይ ፊትዎ ላይ ሜካፕዎ ቢበላሽቦት ይሄ ምርት በቀላሉ የተበላሸቦትን ቦታ ያስተካክሉታል።

ጠቃሚ ምክሮች እንዴት ሜካፕ ኮንሲለር(Makeup Concealer) እንዴት ማቆየት እንደምንችል:

  • ሁልጊዜ ሲገዙ ምርቱን ከቆዳዎ ቀለም ጋር ለማዛመድ አይሞክሩ ከቆዳ ቀለምዎ በትንሹ ነጣ ያለውን ይምረጡ ይህንን የሚያደርጉበት ምክንያት በቆዳዎ ላይ ትንንሽ ነጠብጣብ ምልክቶች ካለብዎት በፊትዎ ላይ እንዳይታይ ወይም ለመደበቅ ይረዳል። ፊትዎ ላይ ያሉት የተለያዩ ምልክቶች ለምሳሌ ማድያት፣ ጥቋቁር ነጠብጣቦች እና ጠባሳዎችን ለመሸፈን ከቆዳዎ ቀለም ጋር በሁለት እጥፍ ነጣ የሚለውን ቢጠቀሙ የተሻለ ነው።

  • ኮንሲለር(concealer) በሚመርጡ ጊዜ ለፊትዎ ምንድን ነው ሊሸፍኑ ወይም ሊደብቁ የፈለጉት እና የሚፈልጉትን የሽፋን ደረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።

  • ምርቱን በእጅዎ ያሙቁት ከመጠቀምዎ በፊት ምርቱን በእጅዎ ያሙቁት ይህ በፊትዎ ላይ ቶሎ ለመሰራጨትና ፊትዎ ላይ ወፍሮ ልድፍ እንዳይል ያደርገዋል።

 
 
 

Comments


Address

83 Lyndarum Dr
Epping, 3076
Australia

Contact

Follow

  • facebook

0488633789

©2017 BY KONJOWITE MAKEUP TUTORIAL. PROUDLY CREATED WITH WIX.COM

bottom of page